Economy

የአዲስ አበባን የታክሲ አገልግሎት ዘመናዊ የሚደርግ ዛይራይድ የተሰኘ የስልክ መተግበሪያ በድጋሚ ስራ መጀመሩን  ዛይቴክ አይቲ ሶሊውሽን አክሲዮን ማህበር ይፋ አደረገ

የአዲስ አበባን የታክሲ አገልግሎት ዘመናዊ የሚደርግ ዛይራይድ የተሰኘ የስልክ መተግበሪያ በድጋሚ ስራ መጀመሩን  ዛይቴክ አይቲ ሶሊውሽን አክሲዮን ማህበር ይፋ አደረገ፡፡

የድርጀቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሀብታሙ ታደሰ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ በአዲስ አበባ ከፍተኛ የሆነ የሜትር ታክሲ እጥረት መኖሩን ተናግረው፤ አዲሱ የስልክ መተግበሪያ ያለአግባብ የሚጠየቁ ክፍያዎችን ከማስቀረት እና ከደህንነት አንጻር ተመራጭ ነው ብለዋል፡፡

ዛይራድ የስልክ መተግበሪያ በተጋጋሚ አዳዲስ ማሻሻያዎች የተደረጉለት ሲሆን በአነስተኛ የኔትወርክ አቅም ጭምር እንዲሰራ ተደርጓል ያሉት የድርጅቱ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስራ አስኪያጅ አቶ በረከት ባይሳ መተግበሪያው ለአጠቃቀም ቀላል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የድርጅቱ የቢዝነስ አማካሪ አቶ ያሬድ ሃይለመሰቀል  በበኩላቸው ቴክኖሎጂው በአለም አቀፍ ደረጃ በርካታ ተጠቃሚዎች ያሉት ሲሆን ግዙፍ ኢኮኖሚ ያንቀሳቅሳል ነው ያሉት ፡፡

ዛይራይድ በአሁኑ ሰዓት 40 ሺ ደንበኞች ያሉት ሲሆን ከ20ሺ ሆቴሎች እና ከ18 በላይ ተቋማት ጋር በኮርፖሬት ይሰራል መባሉንም ሰምተናል፡፡

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button