loading
በዩሮ ማጣሪያ ጣሊያን እና ስፔን ድል ቀንቷቸዋል ::

የማጣሪያ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታዎች ትናንት ምሽት ተከናውነዋል፡፡

በምድብ D ስዊዘርላንድ በሴንት ጃኮብ ዴንማርክን አስተናግዳ ከመምራት ተነስታ በሶስት አቻ ውጤት ተለያይታለች፡፡

አየርላንድ ጆርጂያን 1 ለ 0 አሸንፋለች፡፡

ምድብ F ላይ ስፔን ወደ መካከለኛው ሜድትራኒያኗ ሀገር ማልታ አምርታ ታካሊ ላይ በአልቫሮ ሞራታ ሁለት ግቦች ታግዛ 2 ለ 0 ድል አድርጋለች፡፡

የምድቡን መሪነት በስድስት ነጥብ አጠናክራለች፡፡

ከምድቡ ኖርዌይ ከ ስዊድን 3 ለ 3 አቻ ተለያይተዋል፤ ሮማኒያ የፋሮ ደሴቶችን 4 ለ 1 መርታት ችላለች፡፡

በምድብ J ጣሊያን ታርዲኒ ላይ ሌችተንስታይንን 6 ለ 0 ድል ስታደርግ፤ ፋቢዮ ኳግሊያሬላ በፍፁም ቅጣት ምት ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር፤ ስቴፋኖ ሴንሲ፣ ማርኮ ቬራቲ፣ ሞይሴ ኪን እና ሊዮናርዶ ፓቮሌቲ ከመረብ አገናኝተዋል፡፡

ቦስኒያ ሄርዜጎቪና ከ ግሪክ 2 ለ 2 አቻ ሲለያዩ፤ ፊንላንድ አርሜኒያን 2 ለ 0 አሸንፋለች፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *