EthiopiaPolitics

የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የመጀመሪያ ደረጃ የአደጋ ምርመራ ውጤት ሪፖርት በዛሬው እለት ይፋ ሆነ።

የተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የመጀመሪያ ደረጃ የአደጋ ምርመራ ውጤት ሪፖርት በዛሬው እለት ይፋ ሆነ።

በሪፖርቱም አብራሪዎች አውሮፕላኑን ለመቆጣጠር ያስችላል ብሎ አምራች ኩባንያው ያስቀመጠውን ሂደት መከተላቸው ታዉቋል፡፡

የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የመጀመሪያ ደረጃ የአደጋ ሪፖርትን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ፥ ምርመራው ዓለም አቀፍ ሂደቶችን ተከትሎ መካሄዱን አተናግረዋል።

አደጋው መድረሱን ተከትሎ በትራንስፖርት ሚኒስቴር ስር ያለ የአደጋ ምርመራ ቡድን ስራ ጀምሯል ብለዋል፡፡

የምርመራ ቡድኑ ውስጥም አደጋው የደረሰበት ሀገር ባለሙያዎች፣ የአውሮፕላኑ አምራች ቦይንግ እና የአሜሪካ አቪዬሽን ባለሙያዎች መካተታቸውን እንዲሁም የፈረንሳይ እና የአውሮፓ አቪዬሽን በምርመራው እንዲሳተፉ መደረጉን ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

እስካሁን በተደረገዉ የመጀመሪያ ደረጃ ምርመራ

1ኛ አውሮፕላኑ የፀና መብረር የሚያስችል የምስክር ወረቀት ያለው መሆኑ መረጋገጡ፣

2ኛ አብራሪዎቹ ይህንን በረራ ማድረግ የሚያስችላቸው ብቃትና ፈቃድ እንዳለቸው መረጋገጡ፣

3ኛ አውሮፕላኑ ለበረራ ሲነሳ በትክክለኛ መስመር ለመብረር በሚያስችለው ሁኔታ ላይ እንደነበር እና

4ኛ አብራሪዎቹ አውሮፕላኑን ለመቆጣጠር ያስችላል ብሎ አምራች ኩባንያው ያስቀመጠውን ሂደት ተከትለው አውሮፕላኑን ለመቆጣጠር የሰሩ መሆኑን በምርመራው መገኘቱ አስታውቀዋል።

የምርመራ ቡድኑም የመጀመርያ ደረጃ ምርመራን መነሻ በማድረግ የደህንነት ምክረ ሀሳብ አስቀምጧል፡፡

በዚህም የቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላኖች ላይ ተደጋጋሚ የሆነና አውሮፕላኑን ለመቆጣጠር ያስችገረ የአውሮፕላንን አፍንጫ የመድፈቅ ችግር እንዳጋጠመ  በዚህ የመነሻ ምርመራ በመለየቱ፤ አውሮፕላኑን በበረራ ወቅት ለመቆጣጠር የሚያስችል የበረራ ቁጥጥር ስርዓቱን አምራቹ በድጋሚ ሊፈትሸው ይገባል የሚል ምክረ ሀሳብ በሪፖርቱ ተቀምጧል።

የአውሮፕላን ስሪቱ ወደ በረራ ከመመለሳቸው በፊት የሚመለከታቸው የአቪዬሽን አካላት በበረራ ወቅት የሚያጋጥመውን የመቆጣጠር ችግር የሚያስወግድ የበረራ ቁጥጥር ስርዓት በበቂ ሁኔታ ሊያረጋግጡ እንደሚገባም በምክረ ሀሳቡ ተካትዋል።

የመጀመሪያ ደረጃ የአደጋ ሪፖርቱን መሰረት በማድረግ በመጪው አንድ ዓመት ውስጥ ዝርዝር ሪፖርቱ ለዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ ይፋ እንደሚሆንም ታውቋል።

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button