loading
የኅብረት ሥራ ኤጀንሲ እና የክልሎች ኅብረት ሥራ አበረታች ስራዎች ማከናወናቸው ተገለፀ

የኅብረት ሥራ ኤጀንሲ እና የክልሎች ኅብረት ሥራ አበረታች ስራዎች ማከናወናቸው ተገለፀ

የፌደራል ኅብረት ሥራ ሴክተር የ2011 በጀት ዓመት የ8 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ   በተደረገበት ወቅት እንደተገለፀው  የኅብረት ሥራ ኤጀንሲዎች  እና የክልሎች ኅብረት ሥራ ማህበራት  አበረታች ስራዎች ማከናወናቸው  ተነግሯል፡፡

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዑስማን ሱሩር በ8 ወራት የሴክተሩ አፈጻጸም ጥሩ ውጤት የተመዘገበባቸው መሆናቸውን በመገልፅ፤ ከኅብረት ሥራ ማጠናከር አንጸር ካፒታል በማሳድግ፣ ትርፍ ክፍፍል ከማሻሻል፣ የሀገር ውስጥ ግብይት መነቃቃት ፣ የግብርና ሜካናዜሽን መስፋፋ እና የአግሮ ፕሮሰሲንግ ቁጥር ማደግ፣ እንዲሁም በቁጠባና ኢንቨስትመንት አንጻር ከፍተኛ ለውጥ መመዝገቡን  ተናግረዋል፡፡

በውይይቱ  ወቅት መሻሻል ከሚሹ ጉዳዮች መካካል የኅብረት ሥራ ብቃት ማረጋጋጥ እና ኦዲቲንግ አገልግሎት ረገድ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው በመድረኩ የተነሱ ጉዳዮች  ሲሆን በአጠቃላይ ግን የሴክተሩ አፈጻጸም ከክልል ክልል መለያየት እንዳሳየ በውይይቱ ወቅት ተነሰቷል፡፡

በውይይቱ መጨረሻም በቀሪ ወራት ልዩ ትኩረት የሚሹ ተብለው የተለዩት ጉዳዮች የተገለፁ ሲሆን፤ኅብረት ሥራን ከማጠናከር አንጻር ስልጠናዎች መሰጠት እንደሚገባ እና  የኅብረት ስራ ማህበራትን በባለሙያ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አጽንኦት በመስጠት የምክክር መድረኩ ተጠናቋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *