loading
አቡዳቢ እና ሪያድ ለኢራን የድጋፍ እጆቻቸውን ሊዘረጉ ነው፡፡

አቡዳቢ እና ሪያድ ለኢራን የድጋፍ እጆቻቸውን ሊዘረጉ ነው፡፡

የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች የቀይ ጨረቃ ማህበር በኢራን የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ለደረሰባቸው ሰዎች 95 ቶን የሰብዓዊ እርዳታ ቁሳቁሶችን የጫነ አውሮፕላን ወደ ቴህራን ማቅናቱን ተናግሯል፡፡

እንደ ማህበሩ መግለጫ ይህ ድጋፍ ሳውዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች በትብብር የለገሱት እገዛ ነው፡፡

ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው 1 ሺህ 900 ከተሞችን ባጠለቀለቀው የኢራን የጎርፍ አደጋ 76 ሰዎች ህይዎታቸው ሲያልፍ በጠቅላላው ከ2 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የአደጋው ጉዳት ተጠቂዎች ናቸው፡፡

በአደጋው ሳቢያ ቤት ንብረታቸውን ያጡ 86 ሺህ ኢራናዊያን ወደ ጊዜያዊ መጠለያ በመግባታቸው የረድኤት ድርጅቶችን በቂ የሆነ ሰብዓዊ ድጋፍ ለማቅረብ አቅማቸውን ፈትኖታል ነው የተባለው፡፡

አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለቸው ማእቀብ በርካታ ሀገራትን ኢራንን ከማገዝ ወደ ኋላ እንዳስቀራቸውም በስፋት እየተነገረ ነው፡፡

ከኢራን ጋር ሻካራ የሚባል ግንኙነት ያላት ሳውዲ አረቢያ ከተባሩት አረብ ኤሜሬቶች ጋር በመሆን ለእርዳት አጇን መዘርጋቷ በመጠኑም ቢሆን በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ውጥረት ሊያረግበው ይችላል የሚል ግምት አለ፡፡

መንገሻ ዓለሙ

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *