Ethiopia

በትግራይ እንደተፈፀመ በተሰማው የአየር ጥቃት የተጎዱ ወገኖችን በፍጥነት ወደ ሕክምና ስፍራ ማድረስ አልተቻለም ተባለ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 16፣ 2013 በትግራይ እንደተፈፀመ በተሰማው የአየር ጥቃት የተጎዱ ወገኖችን በፍጥነት ወደ ሕክምና ስፍራ ማድረስ አልተቻለም ተባለ፡፡ ከተጎጂዎቹ መካከል ወደ መቀሌ ሐይደር ሆስፒታል እስካሁን መድረስ የቻሉት አንድ የ2 ዓመት ሕጻን እና 5 አዋቂ ቁስለኞች መሆናቸውን አርትስ ያገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
አርትስ ቲቪ ወደ አካባቢው ደውሎ ለማጣራት ባደረገው ጥረት ከመቀሌ በስተምዕራብ 25 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው እዳጋስሉስ አካበቢ የአየር ድብደባ እንደተፈጸመ በስልክ ያነጋገርናቸውና ማንነታቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የመረጃ ምንጫችን ነግረውናል፡፡

ድብደባው የተፈጸመው በገበያ አካባቢ እንደመሆኑ በርካታ ሰዎች እንደተጎዱ እንደሚገመት እና ከ 40 በላይ የቆሰሉ እንዳሉ መረጃ እንደደረሳቸው እና ወደ ስፍራው ተንቀሳቅሰው ለተጎጂዎች ሕክምና ለመስጠት እና ወደ ሐይደር ሆስፒታል ለማምጣት መከላከያን እየጠየቁ እንደነበረ እና አሁን ወደ ስፍራው ለመድረስ ፍቃዱ ስለተገኘ የሕክምና ቡድን ወደ ስፍራው እንደተላከ የገለፁ ሲሆን፤ እስካነጋገርናቸው ሰዓት ድረስ ወደ ስፍራው የተላኩት የሕክምና ባለሙያዎች ተመልሰው እንዳልመጡ እና በመጠባበቅ ላይ እንዳሉም ገልጸውልናል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button