loading
ኮልፌ አጠና ተራ ታይዋን ሰፈር አካባቢ በደረሰ የእሳት አደጋ 7 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙ ተገለጸ::

አዲስ አበባ፣ የካቲት 24፣ 2014 ኮልፌ አጠና ተራ ታይዋን ሰፈር አካባቢ በደረሰ የእሳት አደጋ 7 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙ ተገለጸ:: አደጋው የደረሰው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታዉ ኮልፌ አጠና ተራ ታይዋን ሰፈር አካባቢ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ ትላንት ምሽት በደረሰው በዚህ የእሳት አደጋ 7 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን የኮሚሽኑ የህዝብ ግኑኝነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ተናግረዋል፡፡


የህዝብ ግንኙነት ባለሙያው አክለውም እሳቱን ለማጥፋት በስፍራው የተገኙ ሁለት የአደጋ ሰራተኞች በጭስ የመታፈን ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው ህክምናቸውን ተከታትለው ረፍት እንዲወስዱ መደረጉን ገልጸዋል፡፡ የኮሚሽኑ ሰራተኞች አደጋውን ለመቆጣጠር ባደረጉት ከፍተኛ ርብርብ 50 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን መቻሉንም አቶ ንጋቱ ተናግረዋል፡፡


አደጋ በደረሰ ቁጥር የእሳት አደጋ ተሽከርካሪዎች መግቢያ መንገድ እያጡ እንደሚቸገሩ የገለጹት አቶ ንጋቱ በዚህኛው አደጋም ተመሳሳይ ችግር ገጥሟች እንደነበር ነው የተናገሩት፡፡ አደጋን ቀድሞ ለመከላከል እንዲቻል ማንኛውም ሰው የንግድም ሆነ ሌሎች ተቋማትን ዘግተው በሚወጡበት ወቅት ለእሳት መነሳት ምክንያት የሚሆኑ ነገሮችን ትኩረት በመስጠት ጥንቃቄ እዲያደርጉም አሳስበዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *