loading
የህንድ ፍርድ ቤት 38 ተከሳሾች በሞት እንዲቀጡ የፍርድ ውሳኔ ማስተላለፉ ተሰማ፡፡

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2014 የህንድ ፍርድ ቤት 38 ተከሳሾች በሞት እንዲቀጡ የፍርድ ውሳኔ ማስተላለፉ ተሰማ፡፡ ግለሰቦቹ ይሙት በቃ የተወሰነባቸው እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2008 ከ50 በላይ ሰዎች የተገደሉበትን የቦንብ ጥቃት አድርሰዋል በሚል ነው፡፡ በጉጂራት ግዛት በምትገኘው የአህመዳባድ ከተማ በደረሰው ጥቃት 56 ሰዎች ሲገደሉ 200 የሚሆኑት የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል ነው የተባለው፡፡


ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ወደ 80 የሚጠጉ ሰዎች ክስ ተመስርቶባቸው የነበረ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 38ቱ በሞት አስራ አንዱ ደግሞ በእድሜ ልክ እስራት መቀጣታቸውን አልጀዚራ በዘገባው አስነብቧል፡፡ ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ያስተላለፈው ተከሳሾቹ በሙሉ በነፍስ ግድያ እና ወንጀልን በጋራ በማሴር ተካፋይ
እንደነበሩ በማስረጃ በማረጋገጡ መሆኑን አብራርቷል፡፡ ከተከሳሾች መካከል 28 ግለሰቦች በወንጀል ድርጊቱ አለመሳተፋቸውን በሚገባ ማስረዳት በመቻላቸው
ፍርድ ቤቱ በነጻ እንዳሰናበታቸው ታውቋል፡፡ ራሱን ኢንዲያን ሙጃሂዲን ብሎ የሚጠራው ቡድን ጥቃቱን ያደረስኩት እኔ ነኝ በማለት ሃላፊነቱን ወስዶ
የነበረ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ በግዛቷ በተቀሰቀሰ አመጽ ለተገደሉ ሙስሊሞች የበቀል እርምጃ ነው ሲል ገልፆ ነበር፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *