loading
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 13ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ ነው

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 13ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን እያካሄደ ነው በጉባኤው ላይ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ የሐይማኖት አባቶች፣ የክልሎችና የከተማ መስተዳድሮች የሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ ተወካዮች ተገኝተዋል። ወይዘሮ ሙፈሪያት የኢትዮጵያ የሐይማኖት ጉባኤ ምዕመናን ችግር ሲገጥማቸው ከችግር የሚወጡበትን መንፈሳዊ ጥንካሬን ሲሰጥ መቆየቱን አንስተዋል፡፡ ይህም ኢትዮጵያ እንደ ሀገር እንድትቀጥል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማድረጉንና ባለፉት ሦስት ዓመታት የገጠሙንን ችግሮች ጸሎትንና የመንፈስ ምግብን እንደ ስንቅ በመያዝ አብረን ተጉዘናል ብለዋል፡፡

ሐይማኖትና መንግሥት በጋራ በመደጋገፍ ሥራዎችን እንደሚሰሩና ጉባኤውም ይህንን አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ እምነታቸው መሆኑን አመልክተዋል።
ያለንበት ወቅት የሰላምና የብልጽግና ጉዞ ለማስቀጠል የምንሰራበት በሌላ በኩል ለዘመናት የተከማቹ ችግሮች የተከሰቱበት በመሆኑ ችግሮቹን በመቅረፍ የትስስር ሰንሰለት የምንቀጥልበትን መንገድ ለመስራት የሐይማኖት አባቶች ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል። ይህንንም ለማድረግ የሐይማኖት አባቶች ሚና ሰፊ ድርሻ ያለው በመሆኑ ፈተናውን በጋራ ጸንቶ ማለፍ ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ አደለም ሲሉም ተናግረዋል።

በጸሎት በምሕላ ኢትዮጵያ ጸንታ የምትቆምበትን መንገድ እንድትሰሩ ያስፈልጋል በማለት አመልክተዋል። የኢትዮጵያ ሐይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሰብሳቢ ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስ በበኩላቸው የሐይማኖት አባቶች እውነተኛ የሰላም ሐዋርያ በመሆን ልንሰራ ይገባናል ብለዋል። የአገር ሰላም በምኞትና ፍላጎት ብቻ አይመጣም፣ ጽኑ ተከታታይና ሰፊ ስራ በመሥራት የሚገኝ ውጤት መሆኑን ልንገነዘብ ይገባናል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *