loading

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 09፣ 2014 በቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በሮጲ ከተማ የተገነባው የኢፋ ሮጲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተመረቀ::የቀዳማዊት እመቤት ጽ/ቤት በ2013 ዓ.ም በሁለተኛ ዙር ግንባታቸዉ ከተጀመሩት ትምህርት ቤቶች መካከል የመጀመሪያ የሆነዉን በኦሮሚያ ክልል ምእራብ አርሲ ዞን ሮጲ ከተማ የኢፋ ሮጲ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ነው ያስመረቀው፡፡ የኢፋ ሮጲ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ በሰባት ወር ጊዜ ዉስጥ የተጠናቀቀ ሲሆን÷ 1ሺህ800 ተማሪዎችን በሁለት ፈረቃ የማስተማር አቅም አለው። በውስጡም አንድ ቤተመጽሐፍ 18 የመማሪያ 4 የላብራቶሪ ክፍሎች እና የአስተዳደር ህንጻ ያካተተ
ነዉ፡፡

ለግንባታው 14 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደተደረገበት ታውቋል፡፡ በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና ሌሎች እንግዶችም ተገኝተዋል። ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ወላጆች እና ወጣቶቹ ለትምህት ቅድሚያ እንዲሰጡ መልዕክትን አስተላልፈው የደብተር፣ ቦርሳና ጫማ ስጦታ ለተማሪዎች አበርክተውላቸዋል። የቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት ከዚህ ቀደም የልዩ ፍላጎት ትምህርት ቤት እድሳትን ጨምሮ በተለያዩ የሃገሪቱ ከፍሎች 20 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ገንብቶ ማስረከቡ
ይታወሳል።

በሁለተኛ ዙር የገነባቸዉን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ማስመረቅ መጀመሩን የገለጸው ጽህፈት ቤቱ የትምህርት ተደራሽነትን ለማገዝ በያዝነዉ አመት የሚጠናቀቁ ሌሎች 7 ትምህርት ቤቶች በመገንባት ላይ መሆናቸውን አስታውቋል።ፅህፈት ቤቱ በአዲስ አበባ ዲቦራ ፋዉንዴሽን ዉስጥ የልዩ ፍላጎት ትምህርት ቤትን፣ በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን አበሽጌ ወረዳ፣ በሲዳማ ክልል ኦዲቦኩ ቀበሌ ፣በጅማ ዞን አኮ ወረዳና በምእራብ ሸዋ አምቦ ጎረምቲ ቀበሌና ሌሎች ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን እየገነባ ሲሆን ÷ አርማጪሆ ማሰሮ ደንብ ወረዳ በቅርቡ ግንባታው እንደሚጀምር አስታውቋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *