loading
ቻይና የጸረ ሚሳኤል ሙከራና የቀጠናው ውጥረት ማገርሸት

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2014 የ ቻይና የተሳካ የመካከለኛ ርቀት የጸረ ባለስቲክ ሚሳኤል ሲስተም ሙከራ ማድረጓን ይፋ አደረገች፡፡ የቻይና መካለከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ሙከራው ቤጂንግ ከየትኛውም አቅጣጫ ሊቃጣባት የሚችለውን የሚሳኤል ጥቃት መከላከል ላይ ያተኮረ ነው ብሏል፡፡ ሙከራው የታቀደለትን ግብ ያሳካ ነበር ያለው ሚኒስቴሩ ዓላማውም መከላከልን እንጂ በየትኛውም ሀገር ላይ ስጋት ለመፍጠር እንዳልሆነ ይታወቅልን ነው ያለው፡፡


ቻይና በህዋ ላይ የሚንቀሳቀሱ ሳተላይቶችን ሊያወድሙ በሚችሉ ሚሳኤሎች ዙሪያ ሰፊ ጥናትና ምርምር እያደረገች መሆኗን አልጀዚራ በዘገባው አስነብቧል፡፡
ከመሬት ወደ አየር የሚወነጨፈው ይህ የጸረ ሚሳኤል ሙከራም የዚሁ መርሃ ግብር አንዱ አካል እንደሆነ ነው የተገለጸው፡፡ ቤጂንግ እነዚህን ምርምሮችና ሙከራዎች የምታደርገው በቀጠናው ካሉ ሀገራት በጦር መሳሪያ ዝግጅቷ አንሳ ላለመታየት መሆኑን የፖለቲካ ምሁራን ተናግረዋል፡፡


ይህም በአካባቢው ያለውን ውጥረት ከመቸውም ጊዜ በባሰ ሁኔታ ከፍ ወዳለ ደረጃ እንዳያሸጋግረው ስጋት ፈጥሯል ነው የተባለው፡፡ ቻይና እንደ አወሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ2010 ወዲህ ባሉት ዓመታት ሶስት ያህል ተመሳሳይ የጸረ ሚሳኤል ሙከራዎችን ማካሄዷ ይታወቃል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *