loading
የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዎንግ ዩ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እና ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ጋር ተወያዩ

በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙትን የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከሁለቱ የሃገሪቱ ታላላቅ ባለስልጣናት ጋር በነበራቸው ውይይት በሁለቱ ሀገራት መካከል ባለው የጠበቀ የረጅም ጊዜ ግንኙነት እና ቻይና ለኢትዮጵያ በምታደርገው ድጋፍ ዙሪያ ተነጋግረዋል።

ዋንግ ዩ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጋር በነበራቸው ቆይታ የኢትዮጵያና የቻይና ግንኙነት ከመሰረተ ልማት እድገት በተጨማሪ የቴክኖሎጂ ትብብር ላይ ሊያተኩር እንደሚገባ ተነጋግረዋል።

የኢትዮጵያ አቅጣጫ በትክክለኛው መንገድ ላይ ይግኛል ያሉት ዋንግ ዩ  ሀገራቸው በሁሉም መስክ ኢትዮጵያ ለምታደርገው የልማት እንቅስቃሴ ትብብር ታደርጋለች ብለዋል።

ከኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር ለመወያየት በብሄራዊ ቤተ መንግስት የተገኙት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቻይናና ኢትዮጵያ በንግድ እና በኢንቨስትመንት ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ማስፋት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል።

በውይይታቸውም ሁለቱ ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነታቸውን ለማስጠበቅ እና ቀጠናዊ ሰላምና መረጋጋትን ለመፍጠር በጋራ በሚሰሩበት ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይም መግባባት ላይ ደርሰዋል።

ቻይና ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥልም ቃል ገብተዋል። መረጃዎቹን ከጠቅላይ ሚኒስትር እና ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት አግኝተናቸዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *