ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ የጥቁር አንበሳ ካንሰር ማዕከልን ጎበኙ
ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በሚገኘው የካንሰር ማዕከል ተኝተው ህክምናቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ ህጻናትና ልጆችን ጎበኙ፡፡
ካንሰር በማህበረሰቡ ላይ እያደረሰ ያለውን ዘርፈ ብዙ ችግር ለመከላከል መላው ህብረተሰብ የሚጠበቅበትን አስተዋጽዎ እንዲጫወትም ፕሬዝደንቷ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሚገኘው የካንሰር ማዕከል 42 የሚደርሱ አልጋዎች ብቻ ቢኖሩትም ተቀብሎ የሚያስተናግዳቸው ህጻናትና ልጆች ግን በየጊዜው ቁጥሩ በከፍተኛ መጠን እያደገ መጥቷል፡፡
ከአልጋ እጥረት በተጨማሪ የካንሰር መድሃኒት እጥረትም የማዕከሉ ዋነኛ ችግር መሆኑን በጉበብኝቱ ወቅት ተገልጿል፡፡
በማዕከሉ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ብቻ በካንሰር የተያዙ 700 የሚደርሱ ህጻናትና ልጆች መመዝገባቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
ከጉብኝቱ በኋላ ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ማዕከሉ ህሙማንን ለመርዳት የሚያደርገው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ጎን ለጎንም ማዕከሉ ያሉበትን ችግሮች ለማየት እንዳስቻላቸው ነው የገለጹት፡፡
ይህ ሁኔታ ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ችግሩን ለመከላከል መረባረብ እንደሚኖርብን የሚያመላክት መሆኑን የጠቀሱት ፕሬዝደንቷ በአንድነት ከተንቀሳቀስን ብዙ ችግሮቻችንን ከአቅማችን በላይ ሊሆኑ አይችሉም ነው ያሉት፡፡
ቀጣዩን የገና በዓል በማስመልከትም ፕሬዝደንቷ ለልጆቹ ስጦታ ማበርከታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል