loading
ሉክሱምበርግ በኢኮኖሚ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ለመስራት ፍለጎቷን ገለጸች።

ሉክሱምበርግ በኢኮኖሚ ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጋር በትብብር ለመስራት ፍለጎቷን ገለጸች

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የሉክሱምበርግ የውጭ ጉዳይና የአውሮፓ ጉዳዮች ሚኒስትር የሆኑትን ዣን አሰልቦርንን በዛሬው ዕለት  በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ሁለቱ ሚኒስትሮች የሁለቱን አገሮች ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ የሃሳብ ልውውጥ አድርገዋል። በተለይ ኢኮኖሚያዊ ትስስሩን ይበልጥ ለማጎልበት የተደራራቢ ቀረጥ ማስወገጃ ስምምነት፣ የአየር ትራንስፖርት ስምምነት እንዲሁም ሉክሱምበርግ በፋይናንስና ባንኪንግ ዘርፍ ያላትን ሰፊ ልምድና ተሞክሮ ለሃገራችን ባለሙያዎች ማካፈል በምትችልበት ሁኔታ ዙሪያ ተወያይተዋል።

እንደውጭ ጉዳይ ገለጻ የሉክሰምበርግ ሚኒስትር በቆይታቸው በሃገራችን የሚገኙ የስደተኛ ካምፖችን ተዘዋውረው የጎበኙ ሲሆን ኢትዮጵያ ስደተኞችን በማስተናገድ ረገድ በቅርቡ ያሳለፈችውን ተራማጅ ውሳኔ አድንቀዋል።

ኢትዮጵያና ሉክሰምበርግ ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኑነት ያላቸው ሲሆን ሉክሰምበርግ ኤምባሲዋን በ2004 ዓም አዲስ አበባ ላይ ከፍታለች። ብራስልስ ያለው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ሉክሰምበርግን ሸፍኖ ይሰራል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *