loading

አቢጃን ላይ እየተካሄደ ባለው የአፍሪካ ከ18 እና ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል አስመዝግበዋል

በኮትዲቯር አዘጋጅነት የሚካሔደው የአፍሪካ 3ኛው ከ18 እና 14ኛው ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ትናንት ምሽት በአቢጃን ስታዲየም በይፋ ተከፍቷል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመክፈቻ ውድድሩ ውጤት አስመዝግቧል፡፡

ከ20 ዓመት በታች በ3000 ሺ ሜትር የፍፃሜ ውደድር ላይ የተሳተፈችው አትሌት አለሚቱ ታሪኩ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ወርቅ ስታስመዘግብ ፀሀይ ሃይሉ ደግሞ የነሐስ ሜዳሊያ አግኝታለች።

በወንዶች በ1500 ሜ የፍፃሜ ውድድር ላይ አትሌት ይሁን ፋንታሁን የብር ሜዳሊያ አሸናፊ ሁኗል።

ከ18 ዓመት በታች በስሉስ ዝላይ ሰንበቴ ሮቢ የብር ሜዳሊያ ለሀገሯ ስታስገኝ፤ በስሉስ ዝላይ ከ20 ዓመት በታች በወንዶች የስሉስ ዝላይ አጁሉ አዱላ 5ኛ ሆና አጠናቅቃለች።

በ10000 ሺ ሜትር ውድድር ላይ የተካፈሉት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ውጤት ሳይቀናቸው ቀርቷል። ኬንያ የወርቅ እና የነሐስ ሜዳሊያ ስታገኝ፤ ዩጋንዳ የብር ሜዳሊያ አሳክታለች። በኢትዮጵያ በኩል ደረጀ አዱኛ 4ኛ እንዲሁም ቢተው አደመ አምስተኛ ሆነው ውድድሩን ጨርሰዋል።

መረጃው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *