loading
የቡሄ ባህል መሰረታዊ ይዘቱን መቀየሩ አሳስቦኛል አለ::

ይህንን ያለዉ የአዲስ አበባ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ነዉ፡፡
በባህል እና ቱሪዝም ቢሮ የጋራ ባህል እሴትዳይሬክተር አቶ አለማየው ጌታቸው የቡሄ ባህል መሰረታዊ ይዘት እየተቀየረ መምጣቱንና ስነቃሎቹም ላይ ጥናት ሊደረግ መሆኑን ለአርትስ ቲቪ ተናግረዋል፡፡
ዳይሬክተሩ ባህል እና ቱሪዝም ቡሄን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ምንም አይነት እንቅስቃሴ አለማደረጉን ገልፀው በመጪው ቡሄ ስነቃላዊ ጥናቶችን ለማድርግ በፌደራል ደረጃ መስሪያ ቤቱ ዝግጅቱን ጨርሷል ብለዋል፡፡
የስነቃል መለዋወጥ ከጊዜ እና የኑሮ ስርዓት መለዋወጥ ጋር የሚጠበቅ ቢሆንም ከባህላዊ ወዝ ማፈንገጡ የቡሄ ክብረ በዓል እንዲደበዝዝ እና ከትውልድ ትውልድ መተላለፉን ስጋት ውስጥ የሚከት እንደሆነ ነው አቶ አለማየሁ ከአርትስ ጋር ባደረጉት ቆይታ የጠቆሙት፡፡
ቡሄ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቶችን አጣምሮ የያዘ ባህል እንደመሆኑ የቱሪስት መስህብ ለማድረግ እንዲሁም ለትውልድ ለማስተላለፍ መገናኛ ብዙሃን እና ባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር የቀስቃሽነት ሚና መጫወት ቢኖርባቸውም፤ የባህሉ ባለቤት የሆነው ህብረተሰቡም የአንበሳውን ድርሻ ስለሚወስድ ሃላፊነቱን እንዲወጣ ዳይሬክተሩ አሳስበዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *