ምክር ቤቱ የአውሮፖ ህብረት 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ላለመታዘብ የያዘውን አቋም ዳግም እንዲመለከት ጠየቀ::
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29 ፣ 2013 ምክር ቤቱ የአውሮፖ ህብረት 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ላለመታዘብ የያዘውን አቋም ዳግም እንዲመለከት ጠየቀ::የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የአውሮፖ ህብረት 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ላለመታዘብ የያዘውን አቋም ዳግም እንዲያጤን ጠየቀ።ምክር ቤቱ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዙሪያ ውይይት ባካሄደበት ወቅት የተደረሰበት የአቋም ላይ መግለጫ መስጠቱን ዋልታ ዘግቧል፡፡
ብረት ምርጫውን ላለመታዘብ የያዘው አቋም ተገቢ ባለመሆኑ ውሳኔውን ዳግም እንዲመለከት ጥሪ አድርጓል።ህብረቱ ከዚህ ቀደም የነበሩ ምርጫዎችን ሲታዘብ እንደነበረው ሁሉ ይህን ምርጫ ሊታዘብ ይገባል ብሏል።መንግስት ከህብረቱ ጋር ተያይዞ የሄደበትን እና የደረሰበት የድርድር ሂደት ግልፅ እንዲያደርግም ጠይቋል።
የአውሮፓ ህብረት በአቋሙ ፀንቶ ምርጫውን አልታዘብም ካለ ግን መንግስት ቃል ከመግባት በዘለለ 6ኛው ምርጫ ነፃ፣ ፍትሀዊና ዴሞክራሲያዊ ማድረግን በተግባር የማሳየት ሃላፊነት አለበት ነው የተባለው።