በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ግጭት የተጠረጠረ አንድ ግለሰብ እና ግለሰቡን ረድተዋል የተባሉ ሶስት የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ
አርትስ 17/03/2011
የቤኒሻንጉል ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሰይፈዲን ሃሩን ለኢዜአ እንዳስታወቁት ፖሊስ ሰሞኑን በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በተከሰተው ግጭት ለሶስት ተማሪዎች ሞትና በሌሎችም ለደረሰው ጉዳት የጠረጠረውን አንድ ግለሰብበቁጥጥር ሥር አውሏል፡፡
ግለሰቡ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ከዋለ በኋላ “ታምሚያለሁ “ በሚል መድኃኒት ለመውሰድ በጸጥታ ሃይሎች ታጅቦ ወደ መኖሪያ ቤቱ ከሄደ በኋላ በመኖሪያ ቤቱ ያስቀመጠውን መሣሪያ በማቀባበል በጸጥታ ኃይሎች ላይጥቃት ለመፈጸም ሙከራ ማድረጉን አስረድተዋል፡፡
የግለሰቡ መኖሪያ ቤት ሲፈተሽ የተለያዩ ሀሰተኛ መታወቂያዎች መገኘታቸውን የጠቆሙት ኮሚሽነር ሰይፈዲን የሚጠቀምበትን ኮምፒዩተር ጨምሮ የጸጥታ ሃይሎች ላይ ጥቃት ለማድረስ የሞከረበት ክለሽንኮብ መሣሪያምበቁጥጥር ሥር መዋሉን አስረድተዋል፡፡
ግለሰቡ “ታምሚያለሁ” በሚል ወደ መኖሪያ ቤቱ እንዲሄድ በመፍቀድ በግለሰቡና በጸጥታ ሃይሎች መካከል ውጥረት እንዲፈጠር አድርገዋል በሚል የተጠረጠሩ ሶስት የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የአሶሳከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡
የአሶሳ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማደር አኑር ሙስጣፋ ለኢዜአ እንዳስታወቁት በከተማው የወረዳ ሁለት መደበኛ ፖሊስ አባላት የሆኑ ሶስት ግለሰቦች ማምሻውን ትጥቃቸውን ፈትተው በቁጥጥር ሥር ውለዋል