ዘንድሮ የአሸንዳ በዓል በትግራይ ክልል በድምቀት ይከበራል አለ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ፡፡
የቢሮው ሃላፊ አቶ ዳዊት ኃይሉ ለአርትስ እንደተናገሩት በዓሉን ለማክበር አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት በመደረግ ላይ ነው ብለዋል፡፡
በዓሉ በዋነኛነት በጎዳና ላይ ትርኢቶች እና ባህላዊ ጭፈራዎች የሚደምቅ ሲሆን የፓናል ውይይት እና የፎቶ አውደርዕይ ፕሮግራሞች ጎን ለጎን እንደሚካሄዱ ኃላፊው ነግረውናል፡፡
በዓሉን ለማክበር የክልሉ ተወላጆች እንዲሁም የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገራት ጎብኚዎች ወደ ክልሉ ያቀናሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል፡፡