loading
የአፍሪካ ህብረት በዚህ ዓመት የአፍሪካ ፓስፖርትን ስራ ላይ አውላለሁ አለ

በአፍሪካ ሀገራት መካከል ነፃ እንቅስቃሴ እንዲኖር ለማድረግ ሲባል ህብረቱ በዚህ የፈረንጆች ዓመት የአፍሪካ  ፓስፖርት መመሪያ ማዘጋጀትና ማተም ላይ እንደሚሰራ ይፋ አድርጓል፡፡

ፓስፖርቱን በመጭው የካቲት ወር በአዲስ አበባ በሚካሄደው 32ኛው የህብረቱ ጉባኤ እንደሚበሰር ይጠበቃል፡፡

የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መህመት በአዲስ ዓመት መልዕክታቸው ‹‹ ዓባል ሀገራቱ በአህጉሪቱ የሀገራት ድንበር በቀላሉ ለመግባትና ለመንቀሳቀስ እየወሰዳችሁት ላለው  እርምጃ አባል ሀገራትን እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለት እወዳለሁ፤ ይህንን ትልቅ ሀውልት ለማቆም በሚደረገው እንቅስቃሴ ውስጥ ያልገባችሁ ሀገራትም ቢሆን በፍጥነት እንድትቀላቀሉን መልዕክቴ ይድረሳችሁ›› ብለዋል፡፡

ፋኪ ሲያጠቃልሉ የአፍሪካ ፓስፖርትን እውን ለማድረግ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ጨምሮ ሀገራቱን በአንድ የሚያስተሳስር የአፍሪካ አየር ትራንስፖርት ገበያ እና የአፍካ አህጉራዊ ነፃ የገበያ ቀጠና ስምምነቶች በበርካታ ሀገራት ይሁንታ ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

የአፍሪካ ህብረት ጉባኤ በየካቲት 19 ቀን2019 ሲከናወን፤ ለአፍሪካ አንድነት ድርጅት መፈጠር መሰረት የጣለውን በፓሪስ የተካሄደውን የፓን አፍሪካን ጉባኤ መቶኛ ዓመት በዓል በማክበር ነው ተብሏል፡፡

 

 

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *