የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫው ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚካሄድ አስታወቀ::
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12፣ 2013 የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫው ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚካሄድ አስታወቀ:: ግንቦት 28 ቀን ሊካሄድ የነበረው ሀገራዊ ምርጫ እንዲራዘም መደረጉ የሚታወስ ሲሆን ቦርዱ ዛሬ በሰጠው መግለጫ ትክክለኛው ቀን መቸ እንደሆነ ይፋ አድርጓ፡፡ በዚህም መሰረት 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም የሚካሄድ መሆኑ ተሰምቷል፡፡
ቦርዱ አክሎም የምርጫ ሂደቱ በሁሉም የመራጮች ምዝገባ በተጠናቀቀባቸው ቦታዎች ብቻ ነው መሆኑን ገልጿል፡፡ ከመራጮች ምዝገባ ጋር አቤቱታ የተነሳባቸው እና ምዝገባውን ዘግይተው የጀመሩ እና ያላጠናቀቁ የምርጫ ክልሎች እና ጣቢያዎች ላይ ግን በዚሁ ቀን አይካሄድም ነው የተባለው።