loading
የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የህግ የበላይነት ተከብሮ ሰላም እንዲረጋገጥ የህዝቡ ተሳትፎ መጠናከር አለበት አለ

የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የህግ የበላይነት ተከብሮ ሰላም እንዲረጋገጥ የህዝቡ ተሳትፎ መጠናከር አለበት አለ

የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ትናንት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ባወጣው መግለጫ ነው ይህንን ያስታወቀው።

በመግለጫውም የመልካም አስተዳደር ችግርን መነሻ በማድረግ በተደረገ ትግል ከፍተኛ መሰዋዕትነት ተከፍሎ የኦሮሞ ህዝብ መብት መረጋገጥ ጀምሯልምብሏል።

በአሁኑ ወቅትም የህዝቡ ተስፋ እየለመለመ መጥቷል ያለው የክልሉ መንግስት፥ ይሁን እንጂ ስልጣን ከእጃቸው የወጣ አካላት በየስፍራው ሴራ በመሸረብ አሁን የተጀመረው ለውጥ እንዲደናቀፍ ሌት ተቀን እየሰሩ ነው ብሏል።

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ከመንግስት ጋር የደረሰው ስምምነት ሙሉ በሙሉ ባለመተግበሩም የኦሮሚያ ክልል ሰላም እየደፈረሰ ነው ብሏል።

በተለይም በአራቱ የወለጋ ዞኖች እና በምእራብ ጉጂ ዞን ውስጥ በየእለቱ የሰው ህይወት እያለፈና ንብረት እየወደመ ነው ያለው የክልሉ መንግስት፥ መንገዶች በመዘጋታቸውና የንግድ እንቅስቃሴ በመቆሙ ህዝቡ ለከፍተኛ ችግር እየተጋለጠ ነው ብሏል።

ወቅቱ ስልጣንን ማእከል በማድረግ እርስ በእርስ ድንጋይ የምንወራወርበት አይደለም ያለው የክልሉ መንግስት፥ ከሁሉም በፊት የህዝቡን ሰላም በማስቀደም ችግሮቻችንን የምንቀርፍበት ጊዜ ላይ ነን ብሏል።

ለአንድነት እና ለሰላም ያለው አማራጭ ህግን ማክበር እና ማስከበር ነው፤ ለዚህ ደግሞ መንግስት ግዳጅ ስላለበት የህግ የበላይነት ተከብሮ ሰላም እንዲሰፍን እየሰራ ነው ብሏል።

ለዚህም ህዝቡ የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ጥሪውን አስተላልፏል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *