የዚምባብዌ መንግስት የተቋዋሚ አባላትን ፍርድ ቤት አቆመ፡፡
ተቃዋሚዎቹ የተከሰሱት በዚምባቡዌ በተካሄደዉ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ኤመርሰን ምናንጋግዋ ማሸነፋቸዉን ተከትሎ በሀገሪቱ በተቀሰቀሰዉ አመጽ እጃችሁ አለበት ተብለዉ ነዉ ፡፡
የኬንያዉ ዴይሊ ኔሽን እንደዘገበዉ 27 የተቃዋሚ ፓርቲ አበላት ላይ የዚምባብዌ አቃቤ ህግ ክስ መስርቶባቸዋል፡፡
ከተከሳሾቹ መካከል ዘጠኙ ሴቶች ናቸዉ ፡፡
ፕሬዝደንቱ በአንድ በኩል የሙቭመንት ፎር ዲሞክራቲክ ቼንጅ ፓርቲን ለአመጹ መነሻ ነዉ በማለት ሲከሱ በሌላ በኩል በግርግሩ ሳቢያ ስለሞቱት ሰዎች ምርመራዉ በአስቸኳይ እንዲከናወን አዘዋል፡፡
በዚምባቡዌ በምርጫዉ ማግስት 6 ሰዎች ከሀገሪቱ የጸጥታ ሀይሎች በተተኮሰ ጥይት መገደላቸዉ ይታወሳል፡፡