ፕሬዝደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ አማራ ክልልን ሊጎበኙ ነው፡፡
በቅርቡ ወደ ኤርትራ ያቀናው የአማራ ክልል ልዑክ ኢሳይያስ አፈወርቂ ክልሉን እንዲጎበኙ በልዩ አማካሪያቸው በኩል ግብዣ አቅርቦላቸዋል፡፡
ፕሬዝደንት ኢሳይያስ አፈወርቂም አማራ ክልልን ለመጎብኘት የቀረበላቸውን ግብዣ መቀበላቸዉን የአማራ መገናኛ ብዘሁን ዘግቧል፡፡
የአማራ ብሄራዊ ክልል ምክር ቤት የልዑክ ቡድን ወደ አስመራ እንዲሄድና የህዝብ ለህዝብ ትስስርን የሚያጠናክር ጉብኝት እንዲካሄድም ተስማምተዋል፡፡
ከምክር ቤቱ ጉዞ በኋላ በፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሚመራ ልዑክ ወደ አማራ ክልል ይመጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡