Africa

ዛኑፒኤፍ አብላጫውን የፓርላማ መቀመጫ አሸንፏል ተብሏል፡

በዚምባቡዌ በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ገዥው ፓርቲ ዛኑ ፒ ኤፍ አብላጫ የፓርላማ ወንበር ማሸነፉ ይፋ ሆኗል፡፡
ሮይተርስና አልጀዚራ ከሀራሬ የሀገሪቱን የምርጫ ኮሚሽን ጠቅሰው እንደዘገቡት ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ የሚመሩት ዛኑ ፒፍ ፓርቲ 109 መቀመጫዎችን ማሸነፍ ችሏል፡፡ ሙቭመንት ፎር ዲሞክራቲክ ቼንጅ የተሰኘው ተቃዋሚ ፓርቲ ደግሞ 41 መቀመጫዎችን አሸንፏል ነው የተባለው፡፡
ቀሪዎቹን 58 መቀመጫዎች ማን እንዳሸነፈ ገና ያልተገለጸ ሲሆን የምርጫ ኮሚሽኑ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያሳውቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የተዋቃዋሚ ፓቲዎች ከምርጫው በፊት ጀምሮ ሲያነሱት የነበረው የምርጫ ኮሚሽኑ በገጠር አካባቢ ምርጫው እንዲጓተት አድርጓል የሚለውን ቅሬታ አሁንም ደግመውታል፡፡
ዚምባቡዌ ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ ሀገሪቱን የገዙትን ሮበርት ሙጋቤን በፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ከተካች በኋላ የመጀመሪያ ምርጫ ነው ያካሄደችው፡፡
ሙጋቤ ለቀድሞ ፓርቲያቸው ዛኑ ፒ ፍ ድምጻቸውን እንደማይሰጡ በምርጫው ዋዜማ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button