loading
ስታን ክሮኤንኬ አርሴናልን ለመጠቅለል አሁንም ጥያቄ አቀረቡ፡፡

በአርሴናል ክለብ ከፍተኛ የአክሲዮን ድርሻ ያላቸዉ ግለሰቡ ክለቡን የግላቸዉ ለማድረግ ጥያቄ አቅርበዋል ተብሏል፡፡
ክሮኤንኬ በአርሴን ቬንገር አሰልጣኝነት ዘመን ለበርካታ አመታት ያለዉጤት የዘለቀዉን አርሴናልን ለመግዛት 600 ሚሊየን ፓዉንድ ማቅረባቸዉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
67 በመቶ የክለቡ ድርሻ ባለቤት የሆኑት አሜሪካዊ ቢሊየነር ከአሁን ቀደም ክለቡን ለመጠቅለል ተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርበዉ አልተሳካላቸዉም፡፡አሁንስ ይሳካላቸዉ ይሆን?
አርሴናል በመጭዉ እሁድ የመጀመርያ የፕሪሜ ርሊግ ጨዋታዉን ከአምናዉ ሻምፒዮን ማንችስተር ሲቲ ጋር ያደርጋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *