Uncategorized

ጣሊያን በሊቢያ የመስፋፋት ሀሳብ የለኝም አለች፡፡

የጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ በሰጡት መግለጫ እኛ ሊቢያ ከምታካሂደዉ ምርጫ በፊት የጸጥታዉን መረጋጋት ለማገዝ እንጂ ድብቅ አጀንዳ የለንም ብለዋል፡፡
ሚድል ኢስት ሞኒተር የሀገሪቱ የመንግስት የቴሌቭዥን ጣቢያን ጠቅሶ እንደዘገበዉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሊቢያ ህገወጥ ስደተኞች ወደ ሀገራችን የሚሸጋገሩባት መስመር በመሆንዋ የአከባቢዉ መረጋጋት በእጅጉ አስፈላጊ እንደሆነ እናምናለን ብለዋል፡፡
ሊቢያ ፖለቲካዊ ፤ስትራቴጂያዊና መልክዓ ምድራዊ ተፈጥሮዋ ከጣሊያን ጋር ያላት ቁርኝት በሀገሪቱ ያለዉን ሁኔታ በቅርበት እንድትከታተለዉና በጋራ እንድንሰራዉ ግድ ይለናል ብለዋል ኮንቴ፡፡
እንደፈረንሳይና ሌሎች በአከባቢዉ ፍላጎት ካላቸዉ ሀገራት ጋርም በትብብር በሊቢያና በሜዲትራንያን ባህር አካባቢ ያለዉን ሠላም የማስጠበቅ ሀላፊነት እንዳለብን ሊታወቅ ይገባል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button