EthiopiaSocial

የኢንጅነር ስመኘው በቀለን ቤተሰቦችን ለመደገፍ የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ተዋቅሯል::

በሀይደሮ ፓወር ዙሪያ የሚያጠኑና ከፍተኛ ዉጤት ለሚያገኙ ተማሪዎች ኢንጅነር ስመኘዉ በቀለ አዋርድ በሚል ለመስጠት እቅድ ተይዟል ተባለ፡፡

የኢንጅነር ስመኘው በቀለን ቤተሰቦችን ለመደገፍ የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ተዋቅሯል::
የመንግስት ኮሙኒኬሽን በድረገጹ እንዳስታወቀዉ ሐምሌ 19 ቀን 2010 ዓ.ም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በመኪናቸው ውስጥ ህይወታቸው አልፎ የተገኙትን የኢንጅነር ስመኘው በቀለን ቤተሰቦች መደገፍ የሚያስችል የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ ተዋቅሯል።
ኮሚቴው ከውሀ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር፣ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ህ/ተ/አስ/ብ/ም/ቤት ጽ/ቤት፣ ከመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት፣ ከኢትዮጵያ ኤሌክሪክ ሀይልና ከኢ/ር ስመኘው በቀለ ቤተሰቦች የተውጣጣ መሆኑን የውሀ መስኖና ኤሌክትሪክ ሚኒስቴር በላከው መግለጫ አስታውቋል።
የሟች ወገኖችን ለመደገፍ በርካታ ወገኖች መጠየቃቸውን ተከትሎ ፍላጎቶችን በአግባቡ ለማስተናገድ እንዲቻል በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ሀይል የበላይ ጠባቂነት በሟች ልጅና ሌሎች ቤተሰቦች በጋራ የሚንቀሳቀስ የባንክ ሂሳብ አካውንት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወጂ ቅርንጫፍ መከፈቱን ከመግለጫው ተመልክተናል።
በዚህም ቤተሰቡን ማገዝ የሚፈልጉ ወገኖች በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወጂ ቅርንጫፍ የሂሳብ ቁጥር 1000254503812 ስመኘው ቤተሰቦች በሚል ድጋፍ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ የኢንጅነር ስመኘው በቀለን ስራዎች ህያው ለማድረግ በሀይድሮ ፓወር ዙሪያ የሚያጠኑና ከፍተኛ ውጤት ለሚያገኙ ተማሪዎች ስመኘው በቀለ አዋርድ በሚል በየአመቱ ሽልማት ለመስጠት በሐይድሮ ፓወር ዙሪያ Acadamic conference እና መሰል ተግባራትን ለመስራት ታቅዷል።

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button