Uncategorized

ኢንዶኔዥያ ዳግም በከባድ ርዕደ መሬት ተመታች፡፡

ኢንዶኔዥያ ዳግም በከባድ ርዕደ መሬት ተመታች፡፡
በዛሬዉ ዕለት ኢንዶኖዥያ ሎምቦክ ደሴት አካባቢ በደረሰ ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ በርካታ ቤቶች ፈራርሰዋል፡፡ነዋሪዎችም አካባቢቸዉን ጥለዉ ሸሽተዋል፡፡
በርዕደ መሬቱ መለኪያ 6.2 እንዲሁም 6.9 የሆነ ተከታታይ የመሬት መንቀጥቀጥ በተከሰተባት ኢንዶኔዥያ 156 ሺህ ዜጎች ቤት አልባ ሆነዋል፡፡
አልጀዚራ እንደዘገበዉ እስካሁን በአደጋዉ ሳቢያ 131 ሰዎች ህይወታቸዉን አጥተዋል፡፡ከሟቾቹ በተጨማሪ ከ1ሺህ 400 በላይ ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
ሰዎቹ ቤት ንብረታቸዉ በመዉደሙ ምክንያትም የምግብ፣የመድሃኒት እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች እጥረት በደሴቷ ተከስቷል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button