EconomyEthiopiaPolitics

በቀጥታ የዘር ግብይት ሥርዓት ከ 1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ማዳን ተቻለ፡፡

የኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሚሽን ኤጀንሲ ከግብርና እንስሳት ሃብት ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን የቀጥታ የዘር ግብይት ሥርዓትን በተመለከተ ውይይት አካሂዷል፡፡
የቀጥታ የዘር ግብይት ስርዓት በማስረጽ ከዚህ በፊት በዘር አከፋፋይ እና በአርሶ አደሩ ይደርስ የነበረውን ችግር እና ውጣውረድ በማስቀረት ዘር አምራቹን ከአርሶ አደሩ ጋር በቀጥታ በማገናኝት ይባክን የነበረውን የሰው ጉልበት እና ሃብት ማስቀረት ተችሏል፡፡
የግብርናና አንስሳት ሃብት ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ዶክተር ኢያሱ አብርሃ እንደተናገሩት በሁለተኛው የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ሀገሪቱ በቀጥታ የዘር ግብይት ሥርዓት ከ 1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ማስቀረት ችላለች፡፡
የዘር ግብይት ስርጭትን መሠረት ካደረገ አሰራር ወደ ፍላጎት ላይ የተመሰረተ የግብይት ስርዓት እንዲሻገር በመደረጉ ያድር የነበረውን የዘር መጠን ከ10 በመቶ በታች እንዲቀንስ አስችሏል ፡፡ በተጨማሪም ያደረ ዘር በተገቢው ማከማቻ በማስቀመጥ ለሚቀጥለው የዘር ወቅት ጥቅም ላይ እንዲውል ማደረግ ተችሏል፡፡
ዶክተር ኢያሱ አርሶ አደሩም በፍላጎት ላይ የተመሠረተ እና ጥራቱን የጠበቀ ዘር በማግኝት የምርት መጠኑን ማሳደግ ችሏል በማለት ተናግረዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button