EconomyEducationEthiopiaSocial

አንድ ሺህ አምስት መቶ የዘንድሮ ተመራቂዎች በአንድ ሰዓት ውስጥ ከቀጣሪዎች ጋር ይገናኛሉ፡፡

ይህ የሚሆነዉ በናሽናል ኬረርስ ኤክስፖ 2018 ነዉ፡፡
የትምህርት ሚኒስቴር ከኢትዮ ጆብስ ጋር በጋራ በመሆን ˝ ናሽናል ኬረርስ ኤክስፖ 2018 ˝ በሚል የዘንድሮ አመት ስራ ፈላጊ ተመራቄዎችን ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር የሚገናኙበት መድረክ በሚሊኒየም አዘገጅቷል፡፡
የኢትዮ ጆብስ ሪጅናል ኮርዲኔተር ወ/ሮ ህሊና ለገሰ ለአርትስ ቲቪ እንደተናገሩት ለመጀመሪያ ግዜ በተዘጋጀው አውደ ርዐዩ ቁጥራቸው አንድ ሺህ አምስት መቶ የዘንድሮ ተመራቂዎች በአንድ ሰዓት ውስጥ ገብተው ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር ይገናኛሉ ፡፡
በዚህ በአይነቱ ለየት ባለው አውደ ርዕይ ከአዲስ አበባና ከክልል ዩንቨርስቲዎች የተውጣጡ 30 ሺ የዘንድሮ አመት ተመራቄዎች ይገኛሉ ፤ለበርካቶችም የስራ ዕድል ያስገኛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በዝግጅቱ የልማት ድርጅቶች፣ ፋብሪካዎች፣ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እና የውጭ ድርጅቶችን ጨምሮ ቁጥራቸው ሁለት መቶ የሚሆኑ ባለሞያ ፈላጊ ድርጅቶች ተሳትፈዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button