loading
አቶ አህመድ ሽዴ የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኢሶህዴፓ/ ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ።

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኢሶዴፓ/ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባለፉት ሶስት ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን ጥልቅ ግምገማ ማጠናቀቁን ተከትሎ ነው አቶ አህመድ ሽዴ ሊቀ መንበር አድርጎ የመረጠው።

የኢሶዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አቶ አህመድ ሽዴን በሙሉ ድምጽ በሊቀ መንበርነት መምረጡም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ኢሶዴፓ/ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባለፉት ሶስት ቀናት ስብሰባው በክልሉ ተፈጥሮ በነበሩው ሁኔታ ላይ ጥልቅ መገምገሙም ተነግሯል።

ክልሉ በቀጣይም የተረጋጋና ሰላማዊ ለማድረግ ጠንክሮ እንደሚሰራም የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አስታውቋል።
ኤፍ.ቢ.ሲ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *