loading
የህወሀት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን መቐለ በተካሄደው ሰልፍ ባስተላለፉት መልእክት “ያለን አማራጭ ተከባብሮ መኖር አልያም መበታተን” ማለታቸው ትግራይን ለመገንጠል ከሚል የመነጨ ሳይሆን የሀገሪቱ የፌደራል ስርአት እኩልነትን መሰረት ያደረገ መሆኑ ለመጠቆም የተነገረ ነዉ አሉ።

ህወሀት በዚህ ወር 13ኛ ድርጅታዊ ታሪካዊ የለውጥ ጉባኤ ያካሄዳል ተብሏል፡፡
ሊቀመንበሩ በጉባኤው እስካሁን የተደረጉት የለውጥ እንቅስቃሴዎች ወደተግባር ሊለውጥ የሚችል ብቁ አዲስ ትውልድ ወደ አመራርነት ይመጣል ብለዋል።
ህወሓት ህገመንግስትን መሰረት አድርጎ ለሚደረግ የለውጥ ጉዞ ደጋፊ እንጂ እንቅፋት እንደማይሆን ዶክተሩ ተናግረዋል።
በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ የሰጡት ሊቀመንበሩ ባለፉት አመታት በሀገሪቱ ከተመዘገቡ የልማት ስኬቶች በተጨማሪ በርካታ ጉድለቶች ታይተዋል ብለዋል።
ይህንንም መሰረት በማድረግ የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልጋል ብሎ በመወሰን ለሌሎች የኢህአዴግ እህት ድርጅቶች ምሳሌ የሆነ ጥልቅ ግምገማ አካሂዶ የተለያዩ ውሳኔዎችን ማሳለፉን እና እርምጃዎች መወሰዱን አስታውሰዋል።
ዶክተር ደብረፅዮን በመግለጫቸው የህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ በወሰነው መሰረት ድርጅቱ ለውጥ ለማምጣት በሚያስችለው አቋም ላይ እንደሚገኝ እና ምሁራን በስፋት በክልላቸው ጉዳይ ላይ እንዲሳተፉ የሚያስችል ዕድል ተመቻችቶ የተለያዩ የጥናት ውጤቶችን ወደ ተግባር ለመለወጥ በመንቀሳቀስ ላይ ነን ብለዋል። ምንጭ ፋና

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *