loading
ለስደተኞች ስራ በማትሰጠው ለንደን ወጣቱ ሲቪውን ይዞ ጎዳና ላይ ለመቆም ተገዷል ፡፡

ሞሀመድ ኤልባራዲ ይባላል፡፡ የ22 ዓመት ወጣት ነው፡፡ ከሊቢያ ተሰዶ መኖሪያውን ለንደን ያደረገው ኤልባራዲ ከለንደን ዩንቨርሲቲ ኮሌጅ በኤሮስፔስ ሳይንስ በማስተርስ ዲግሪ ተመርቋል፡፡
ሆኖም ከ70 በላይ በሚሆኑ ቀጣሪ ድርጅቶች ውስጥ የስራ ማመልከቻ ቢያስገባም አንዳቸውም ምላሽ አልሰጡትም፡፡
በዚህ ሁኔታ የተማረረው ኤልባራዲ ታዲያ በመጨረሻ አንድ ሀሳብ መጣለት፡፡ ስራ እንደሚፈልግ የሚጠቁም ማስታወቂያ ይዞ ሰው በሚበዛበት አካባቢ መቆም፡፡
እናም ይህ ወጣት ስራ ፈላጊ” ወደዚህ ሀገር የመጣሁት በስደት ነው፣ በለንደን ዩንቨርሲቲ ኮሌጅ በሮኬት ሳይንስ ተመርቄያለሁ፣ ስራ ፈላጊ ነኝ ከፈለጋችሁ ሲቪየን ጠይቁኝ ” የሚል ጸሁፍ ይዞ ለንደን ውስጥ በሚገኘው ካናሪ ዋርፍ በተባለው የመሬት ውስጥ የባቡር ጣቢያ ሲቆም የብዙዎችን ቀልብ ስቧል፡፡
ሜሪ ኢንግልኸርት የተባለች ሴት በትዊተር ገጿ ዘመናዊ ነኝ የሚል ሞሀመድን መቅጠር አለበት የሚል ሀሳብ ያለው በፅሁፍ አስፍራለች፡፡
እስካሁን 24,000 ሰዎች ላይክ አድርገውታል፡፡ 16,000 ሰዎች ደግሞ አስተያየታቸውን ሰጥተውበታል፡፡
ኤልባራዲም በርካታ የተቋም ሃላፊዎች አነጋግረውኛል፡፡ የትምህረት ዝግጅቴ ከፍላጎታቸው ጋር ከተስማማ ይቀጥሩኛል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *