loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በጥቅምት ወር መጨረሻ ለይ ጀርመን ሊጓዙ ነው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ ከጀርመኗ ቻንስለር መራሂተ መንግስት ወይዘሮ አንግላ መርከል ጋር በስልክ አውርተዋል፡፡
የጠቅለይ ሚንስቴር ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ በገፃቸው እንዳስነበቡት ቻንስለር መርከል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባጭር ጊዜ እያካሄዱ ላሉት የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሪፎርም ስራዎች በተለይም ከኤርትራ ጋር ለተፈጠረው ሰላም አድናቆታቸውን በመግለጽ እንኳን ደስ ያለዎት ብለዋቸዋል፡፡
ቻንስለሯም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ ጀርመን ተገኝተው በአፍሪካ እና በአውሮፓ ጉዳዮች ላይ እንዲመክሩ የጋበዟቸው ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ግብዣውን መቀበላቸውን አረጋግጠውላቸዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *